ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጉባኤ ላይ በዘርፉ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፈሉ

On Sep 11, 2020 397 አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቪዲዮ በተካሄደው የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጉባኤ ላይ ተሳተፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ፈጠራ የታከለበት እንዲሆን ለማስቻል ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅ በዚህ ጉባኤ ላይ አንስተዋል። እስካሁንም ቢሆን በነበሩ ጠንካራ ጎኖች ላይ በመመርኮዝ በአስደናቂ ሁኔታ በዘርፉ ገስግሰናል ነው ያሉት። በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ አማካኝነት፣ የመንግሥት መዋዕለ ንዋይ ከተጠናከረ የግል ዘርፍ ተሳትፎ ጋር ተዳምሮ የግብርናውን ዘርፍ ግሥጋሴን እንደሚያፋጥን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከቪዲዮ ኮንፍረንሱ በኋላ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ አስተባባሪነት በተካሄደው የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጉባኤ ላይ ጠቃሚ እሳቤዎችን ለማጋራት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። Let's block ads! (Why?)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጉባኤ ላይ በዘርፉ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፈሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቪዲዮ በተካሄደው የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጉባኤ ላይ ተሳተፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ፈጠራ የታከለበት እንዲሆን ለማስቻል ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅ በዚህ ጉባኤ ላይ አንስተዋል።

እስካሁንም ቢሆን በነበሩ ጠንካራ ጎኖች ላይ በመመርኮዝ በአስደናቂ ሁኔታ በዘርፉ ገስግሰናል ነው ያሉት።

በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ አማካኝነት፣ የመንግሥት መዋዕለ ንዋይ ከተጠናከረ የግል ዘርፍ ተሳትፎ ጋር ተዳምሮ የግብርናውን ዘርፍ ግሥጋሴን እንደሚያፋጥን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከቪዲዮ ኮንፍረንሱ በኋላ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ አስተባባሪነት በተካሄደው የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጉባኤ ላይ ጠቃሚ እሳቤዎችን ለማጋራት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

Let's block ads! (Why?)