ኮንዶሚንየም ተመዝግበው ዕጣ ለሚጠባበቁ አዲስ አማራጭ ቀረበ

በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳስታወቁት ለ40/60ና 20/80 ኮንደምንየም ተመዝግበው ዕጣ እስኪደርሳቸው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች መሬት ከአስተዳደሩ በሊዝ ተቀብለው በመደራጀት የራሳቸው የጋራ መኖርያ መገንባት እንዲችሉ አማራጭ ሊቀርብ ነው። በአሁኑ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተመዝጋቢዎች ዕጣ በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም የኮንደምንየም ቤቶች ይገባኛል ጥያቄ አወዛጋቢ እየሆነ በመምጣቱ በእጣ አወጣጥ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖን ፈጥሯል። ሆኖም ቆጣቢዎች መሬቱ ተሰጥቷቸው በራሳቸው ገንዘብ እንዲገነቡ እድል መስጠት ከጅምሩ የጋራ መኖርያ ቤቶች ዋነኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ታስቦ በነበረው አነስተኛ ገቢ ያለው ሕብረተሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን የሚያሳድር ሲሆን በአንፃሩ ገንዘብ በእጃቸው ለያዙ ነዋሪዎች ዕድል የሚሰጥ ይሆናል። የጋራ ኮንደምንየም ቤቶች ግንባታ ፅንሰ ሃሳብ በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ያለውን ሕብረተሰብ የቤት ባለቤት ለማድረግ ያለመ ሆኖ ብዙዎችን የቤት ባለቤት ሊያደርግ ችሎ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትላንትናው ዕለት ኢዜማ ፓርቲ አደረኩት ባለው ጥናት መሠረት በአዲስ አበባ ሰፊ የሆነ የመሬት ወረራና የጋራ ኮንደምንየም አለ አግባብ እደላ መከናወኑን ደርሼበታለው ሲል መግለፁ ይታወሳል።

ኮንዶሚንየም ተመዝግበው ዕጣ ለሚጠባበቁ አዲስ አማራጭ ቀረበ

በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳስታወቁት ለ40/60ና 20/80 ኮንደምንየም ተመዝግበው ዕጣ እስኪደርሳቸው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች መሬት ከአስተዳደሩ በሊዝ ተቀብለው በመደራጀት የራሳቸው የጋራ መኖርያ መገንባት እንዲችሉ አማራጭ ሊቀርብ ነው። በአሁኑ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተመዝጋቢዎች ዕጣ በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም የኮንደምንየም ቤቶች ይገባኛል ጥያቄ አወዛጋቢ እየሆነ በመምጣቱ በእጣ አወጣጥ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖን ፈጥሯል። ሆኖም ቆጣቢዎች መሬቱ ተሰጥቷቸው በራሳቸው ገንዘብ እንዲገነቡ እድል መስጠት ከጅምሩ የጋራ መኖርያ ቤቶች ዋነኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ታስቦ በነበረው አነስተኛ ገቢ ያለው ሕብረተሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን የሚያሳድር ሲሆን በአንፃሩ ገንዘብ በእጃቸው ለያዙ ነዋሪዎች ዕድል የሚሰጥ ይሆናል።

የጋራ ኮንደምንየም ቤቶች ግንባታ ፅንሰ ሃሳብ በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ያለውን ሕብረተሰብ የቤት ባለቤት ለማድረግ ያለመ ሆኖ ብዙዎችን የቤት ባለቤት ሊያደርግ ችሎ ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትላንትናው ዕለት ኢዜማ ፓርቲ አደረኩት ባለው ጥናት መሠረት በአዲስ አበባ ሰፊ የሆነ የመሬት ወረራና የጋራ ኮንደምንየም አለ አግባብ እደላ መከናወኑን ደርሼበታለው ሲል መግለፁ ይታወሳል።