ኢትዮጵያ ለ20 በመቶ ዜጎቿ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለመስጠት ዝግጅት እያደረገች ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባት ማስገባት የሚያስችሉ የላቦራቶሪና ሌሎች ዝግጅቶችን ስታጠናቅቅ 20 በመቶ ዜጎቿ ላይ ክትባቱን እንደምትጀምር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ አስታወቁ። ክትባቱ መስጠት ሲጀመር ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎችና ዳር ድንበር የሚጠብቁ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ ያገኛሉ ብለዋል። የተለያዩ ሀገራት እስካሁን ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን እያፈላለጉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ክትባትን እንደ አንድ መፍትሔ በመውሰድ ለሕዝቦቻቸው ተደራሽ እያደረጉ ነው። እንደ ወይዘሮ ሳህረላ ገለጻ ኢትዮጵያም ሳይንሳዊ ሁኔታዎችን ተከትላ ክትባቱን ለማስገባት ስትዘጋጅ መቆየቷን ገልፀዋል። ይህንን ታሳቢ በማድረግም ክትባቱን መፈተሻ ላቦራቶሪ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት እየተገጣጠመ ይገኛል ብለዋል። ክትባቱ ወደ ሀገር ቤት ከመግባቱ በፊት የላቦራቶሪ ፍተሻዎችን ሲያልፍ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ በዓለም ጤና ድርጅት ለሚመራው የክትባት ድጋፍ ሰጪ ተቋም “ኮቫክስ” የቦርድ አባል መሆኗን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ዜጎችን መከተብ የሚያስችል ድጋፍና ግብዓቶችን ለማግኘት እንደሚረዳት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ሀገሪቷ ለማስገባት ካሰበችው ከጠቅላላው 20 በመቶው ክትባት በግዥና ከለጋሾች ለማሟላት ታሳቢ መደረጉን ገልጸው፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋይናንስ እጥረትን ለመፍታት ቃል የገቡ ሀገራት መኖራቸውን አክለዋል። ሚኒስትር ዴኤታዋ ክትባቱን እንደ ሀገር ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ማድረግ የማይቻልበት ሁኔታ ሰፊ እንደሆነም ተናግረው፤ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ እንደ ሕክምና ባለሙያዎችና ዳር ድንበር የሚጠብቁ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ ሊሰጥ ይችላል ብለዋል። ድጋፉ ከለጋሽ ድርጅቶች ሲጘኝ ለሁሉም ዜጎች በተለያየ ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራም ነው የተናገሩት። ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳ የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን! Let's block ads! (Why?)

ኢትዮጵያ ለ20 በመቶ ዜጎቿ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለመስጠት ዝግጅት እያደረገች ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባት ማስገባት የሚያስችሉ የላቦራቶሪና ሌሎች ዝግጅቶችን ስታጠናቅቅ 20 በመቶ ዜጎቿ ላይ ክትባቱን እንደምትጀምር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ አስታወቁ።

ክትባቱ መስጠት ሲጀመር ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎችና ዳር ድንበር የሚጠብቁ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ ያገኛሉ ብለዋል።

የተለያዩ ሀገራት እስካሁን ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን እያፈላለጉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ክትባትን እንደ አንድ መፍትሔ በመውሰድ ለሕዝቦቻቸው ተደራሽ እያደረጉ ነው።

እንደ ወይዘሮ ሳህረላ ገለጻ ኢትዮጵያም ሳይንሳዊ ሁኔታዎችን ተከትላ ክትባቱን ለማስገባት ስትዘጋጅ መቆየቷን ገልፀዋል።

ይህንን ታሳቢ በማድረግም ክትባቱን መፈተሻ ላቦራቶሪ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት እየተገጣጠመ ይገኛል ብለዋል።

ክትባቱ ወደ ሀገር ቤት ከመግባቱ በፊት የላቦራቶሪ ፍተሻዎችን ሲያልፍ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በዓለም ጤና ድርጅት ለሚመራው የክትባት ድጋፍ ሰጪ ተቋም “ኮቫክስ” የቦርድ አባል መሆኗን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ዜጎችን መከተብ የሚያስችል ድጋፍና ግብዓቶችን ለማግኘት እንደሚረዳት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሀገሪቷ ለማስገባት ካሰበችው ከጠቅላላው 20 በመቶው ክትባት በግዥና ከለጋሾች ለማሟላት ታሳቢ መደረጉን ገልጸው፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋይናንስ እጥረትን ለመፍታት ቃል የገቡ ሀገራት መኖራቸውን አክለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ክትባቱን እንደ ሀገር ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ማድረግ የማይቻልበት ሁኔታ ሰፊ እንደሆነም ተናግረው፤ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ እንደ ሕክምና ባለሙያዎችና ዳር ድንበር የሚጠብቁ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ ሊሰጥ ይችላል ብለዋል።

ድጋፉ ከለጋሽ ድርጅቶች ሲጘኝ ለሁሉም ዜጎች በተለያየ ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራም ነው የተናገሩት።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳ

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Let's block ads! (Why?)