አዋሽ ባንክ ያስመዘገበው ትርፍ ካለፈው ዓመት በ900 ሚልዮን ብር ጨምሯል

ባሳለፍነው 2011 ዓ.ም የ3.3 ቢልዮን ብር ትርፍ አስመዝግቦ የነበረው አዋሽ ባንክ ሊገባደድ ጥቂት ቀናት በቀሩት 2012 የ4.2 ቢልዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የባንኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፀሃይ ሽፈራው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት የአዲስ አመት መልዕክት ላይ ገልፀዋል። አዋሽ ባንክ ዘንድሮ ያስመዘገበው ትርፍ ካለፈው ዓመት የ900 መቶ ሚልዮን ብር ጭማሬ ያሳየ ሲሆን ባንኩ ለመንግስት የሚከፍለው ግብር ከዚህ ትርፍ ላይ የሚቀነስ ይሆናል። ይህ የዘንድሮው ትርፍ ከ2011 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር የ27 ፐርሰንት እድገት ያሳየ ቢሆንም ዘንድሮ የተመዘገበው የ20 ፐርሰንት የዋጋ ግሽበት ከግምት ውስጥ ሲገባ በዛው መጠን የብር የመግዛት ዋጋ የሚሸረሸር በመሆኑ አዋሽ ባንክ ያሳየው የትርፍ እድገት ጭማሬ ካለፈው ዓመት በ7 ፐርሰንት ብቻ የሚበልጥ ነው። በ1988 ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመርያው የግል ባንክ ሆኖ በ486 ባለ አክስዮኖች የተቋቋመው አዋሽ ባንክ ዛሬ ከ4,300 በላይ የአክስዮን ባለቤቶች ያሉት ሲሆን ከ1 ዓመት በፊት በ12 ቢልዮን ብር ወጪ ሜክሲኮ አካባቢ ለዋና መስርያ ቤትነት የሚያገለግል ባለ 50 ደረጃ ህንፃ ማሰራት መጀመሩን አስታውቆ ነበር።

አዋሽ ባንክ ያስመዘገበው ትርፍ ካለፈው ዓመት በ900 ሚልዮን ብር ጨምሯል

ባሳለፍነው 2011 ዓ.ም የ3.3 ቢልዮን ብር ትርፍ አስመዝግቦ የነበረው አዋሽ ባንክ ሊገባደድ ጥቂት ቀናት በቀሩት 2012 የ4.2 ቢልዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የባንኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፀሃይ ሽፈራው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት የአዲስ አመት መልዕክት ላይ ገልፀዋል። አዋሽ ባንክ ዘንድሮ ያስመዘገበው ትርፍ ካለፈው ዓመት የ900 መቶ ሚልዮን ብር ጭማሬ ያሳየ ሲሆን ባንኩ ለመንግስት የሚከፍለው ግብር ከዚህ ትርፍ ላይ የሚቀነስ ይሆናል።

ይህ የዘንድሮው ትርፍ ከ2011 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር የ27 ፐርሰንት እድገት ያሳየ ቢሆንም ዘንድሮ የተመዘገበው የ20 ፐርሰንት የዋጋ ግሽበት ከግምት ውስጥ ሲገባ በዛው መጠን የብር የመግዛት ዋጋ የሚሸረሸር በመሆኑ አዋሽ ባንክ ያሳየው የትርፍ እድገት ጭማሬ ካለፈው ዓመት በ7 ፐርሰንት ብቻ የሚበልጥ ነው።

በ1988 ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመርያው የግል ባንክ ሆኖ በ486 ባለ አክስዮኖች የተቋቋመው አዋሽ ባንክ ዛሬ ከ4,300 በላይ የአክስዮን ባለቤቶች ያሉት ሲሆን ከ1 ዓመት በፊት በ12 ቢልዮን ብር ወጪ ሜክሲኮ አካባቢ ለዋና መስርያ ቤትነት የሚያገለግል ባለ 50 ደረጃ ህንፃ ማሰራት መጀመሩን አስታውቆ ነበር።