"ኑ ጭቃ እናቡካ የጥበብ ማዕከል 2ኛዉኝ የባለእጆች ባዛር በማዕከሉ አዘጋጅቷል

"ኑ ጭቃ እናቡካ የጥበብ ማዕከል 2ኛዉኝ የባለእጆች ባዛር በማዕከሉ አዘጋጅቷል። ባለእጅ የሆናችሁ ሁሉ ያለላችሁን ሙያ አሳዩ እንዲሁም ሽጡ ። ያለንን ውስን የመሸጫ ጠረጴዛ ያዙ እንላለን ። ወላጆች ልጆቻችሁ ለገበያ የሚበቃ ነገር ከሰሩ ለእነሱ ያዘጋጀነውን ባታ ያዙላቸው የተለያዩ ባለእጆች ያበጇቸውን የእጅ ስራዎቻቸውን ይዘው መጥተው እንዲሸጡ፣ በሌላ እንዲለውጡ ወይም እንዲገዙ እንዲሁም አዳዲስ ባለእጆችን እንዲያበረታቱ ልዩ የባለእጆች ኩነት ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ። በባዛሩ ተበልተው የማይጠገቡ የፃም ምግቦች ከተለያዩ የጨዋታ እና መዝናኛ ዝግጅቶች ጋር ይጠብቋችኋል ሚያዝያ 9 እስከ 17 ለተከታታይ 9 ቀናት የሚቆይ በሚገርም ቅናሽ ለፋሲካ በዓል ማስታወሻ እና ስጦታ የሚሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶችን ሸምቱ ። ተጫወቱ !! In @ Nu_Chika_Enabuka