በምስራቃዊ ኮንጎ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የ50 ሰዎች ህይወት አለፈ

An artisanal miner carries raw ore at Tilwizembe, a former industrial copper-cobalt mine, outside of Kolwezi, the capital city of Lualaba Province in the south of the Democratic Republic of the Congo, June 11, 2016. REUTERS/Kenny Katombe On Sep 12, 2020 10 አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ቢያንስ የ50 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል። የአደጋው መንስኤ በአካባቢው የዘነበው ከባድ ዝናብን ተከትሎ ሰዎቹ ሲቆፍሩት የነበረው ጉድጓድ በመደርመሱ ነው ተብሏል። በኮንጎ ቁጥጥር በማይደረግባቸው የማዕድን ማውጫዎች የሚከሰቱ አደጋዎች የተለመዱ መሆናቸው ይነገራል። በዚህምበየዓመቱ የማዕድን ማውጫዎች በመደርመሳቸው ሰዎች ለህልፈት ይዳረጋሉም ተብሏል። በባለፈው አመት ጥቅምት ወር በሀገሪቱ በተፈጠረ ተመሳሳይ አደጋ 16 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ÷ በዚያው ዓመት ሰኔ ወር በመዳብ እና ብረት ማዕድን ማውጫ ላይ በተከሰተ ሌላ የመሬት መንሸራተት አደጋ ደግሞ 43 ሕገ-ወጥ የማዕድን ሠራተኞች መሞታቸው የሚታወስ ነው። ምንጭ፡- ሲጂቲኤን እና ሮይተርስ #FBCየዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ። Let's block ads! (Why?)

በምስራቃዊ ኮንጎ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የ50 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ቢያንስ የ50 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።

የአደጋው መንስኤ በአካባቢው የዘነበው ከባድ ዝናብን ተከትሎ ሰዎቹ ሲቆፍሩት የነበረው ጉድጓድ በመደርመሱ ነው ተብሏል።

በኮንጎ ቁጥጥር በማይደረግባቸው የማዕድን ማውጫዎች የሚከሰቱ አደጋዎች የተለመዱ መሆናቸው ይነገራል።

በዚህምበየዓመቱ የማዕድን ማውጫዎች በመደርመሳቸው ሰዎች ለህልፈት ይዳረጋሉም ተብሏል።

በባለፈው አመት ጥቅምት ወር በሀገሪቱ በተፈጠረ ተመሳሳይ አደጋ 16 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ÷ በዚያው ዓመት ሰኔ ወር በመዳብ እና ብረት ማዕድን ማውጫ ላይ በተከሰተ ሌላ የመሬት መንሸራተት አደጋ ደግሞ 43 ሕገ-ወጥ የማዕድን ሠራተኞች መሞታቸው የሚታወስ ነው።

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን እና ሮይተርስ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Let's block ads! (Why?)